Skip to content
Home » ስለ ድርጅታችን

ስለ ድርጅታችን

አላማችን

በችግር ምክንያት ተገፍተዉ በየጎዳናዉ ከነልጆቻቸዉ ወድቀዉ የነበሩትን እናቶችና ህፃናትና ከጎዳና አንስተን እንደ ማንኛዉም ሰዉ መሰረታዊ ፍላጎታቸዉ ተሟልቶላቸዉ እንዲኖር ማድረግ ነዉ፡፡

ተልዕኳችን

ከቤተሰቦች ፣ ከማህበረሰቦች እና ከሌሎች የፕሮግራሙ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እነዚህን የማህበረሰብ አካላት  የኑሮ ደረጃቸውን  ለማሻሻል  ከድህነት ፣ ስቃይ እና እጦት ለማላቀቅ  የሚቻለውን ጥረት ሁሉ ማድረግ ፡፡

ራዕያችን

ተጋላጭ ፣ ጥገኛ ፣ የተጎዱ እና ችላ የተባሉ ሕፃናትና ሴቶች ከከባድ ድህነት ወጥተው ገለልተኛና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ማስቻል ፡፡

እሴቶቻችን

እነዚህ እሴቶቻችን ስለእኛ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ነገር የሚያንፀባርቁ እና የድርጅታችንን ባህል እና የተመሠረትንበትን ዓላማ የሚያሳዩ ናቸው ፡፡

  1. ሀሳብ አመንጪነት አዳዲስ ሀሳቦችን እና ገንቢ አስተያየትን እንቀበላለን፡፡
  2. ግልጸኝነት እውነተኛ እና ግልጽ መሆን ለእኛ ዋናችን ነው፡፡
  3. ቅልጥፍና ጊዜን ወይም ገንዘብን በአግባቡ እንጠቀማለን፡፡
  4. በጊዜ ያልተገደበ ሁልጊዜም ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ እንተጋለን፡፡
  5. ቅንነት መሥራት ያለብንን ሁሉ በቅንነት መስራታችንን እንቀጥላለን፡፡
  6. ውጤታማነት ማንኛውንም ግብአቶች በአግባቡ ተጠቅመን ውጤትን እናመጣለን፡፡
  7. ሐቀኝነት ምንም ያህል ከባድ ቢሆንም ሁልጊዜ ለእውነቱ እንቆማለን፡፡
  8. ጥራት በስራችን ሁሉ ጥራትን እንመርጣለን ፡፡
  9. በትምህርት ላይ የተመሠረተ ሁሌም እየተማርን እና እናድጋለን ፡፡
  10. ሙያዊነት ሙያዊ ግዴታቸንን በአግባቡ እንወጣለን ሙያችንንም እናከብራለን ፡፡